ዘመን ባስ ኢትዮጵያ ከዱራሜ – አዲስ አበባ በይፋ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
የጉዞ መስመሩ መጀመር በዞኑ የትራንስፖርት ዘርፍ ላይ አዎንታዊ አስተዋጽዖ እንደሚኖረውም ተጠቁሟል።
ድርጅቱ በዱራሜ ከተማ የትኬት ሽያጭ ቢሮ ከፍቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስመልክቶ አስተያየት የሰጡት የዘመን ባስ ማርኬቲንግ ማናጀር አቶ ብሩክ ቦጃ ዘመን ባስ በትራንስፖርቱ ዘርፍ ምቾት ያለው አገልግሎት በመስጠት ለደንበኞች እርካታ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ጠቅሰው የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት ከዱራሜ ወደ አዲስ አበባ አዲስ የጉዞ መስመር መጀመሩን ገልፀዋል።
ዘመን ባስ ኢትዮጵያ ከሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ከዱራሜ – አዲስ አበባ እንዲሁም ከአዲስ አበባ – ዱራሜ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ በዱራሜ ከተማ ኡቱቢ ወጋ አደባባይ ባለው የትኬት ሽያጭ ቢሮ በአካል በመምጣት ወይንም ባሉበት ሆነው በስልክ መስመር 6162 በመደወል አገልግሎት ማግኘት እንደሚቻል አቶ ብሩክ አስረድተዋል።
የዘመን ባስ ኢትዮጵያ በዱራሜ ከተማ አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ መደስታቸውን የገለፁት አንዳንድ የከተማው ነዋሪዎች ከዚህ በፊት አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ አጎራባች ከተሞች በመሄድ ለተጨማሪ ጊዜና ለተጨማሪ ወጪ ሲዳረጉ መቆየታቸውን ጠቅሰው አገልግሎቱ ወደ ከተማዋ መምጣቱ እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል።
ለበለጠ መረጃ
በ0961626262
በ0961202020 ወይንም
በ6162 በመደወል ካሉበት ሆነው ትኬት መቁረጥ ይችላሉ።
#ዘመን ባስ በምቾት የሚያደርስ!

