የሰው ኃይል አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
የዳይሬክቶሬቱ የሥራ ዝርዝር ተግባራት :
የሰው ኃይልን ማሟላት:- በመ/ቤቱ ካሉ ዳይሬክቶሬቶች የሰው ኃይል ማሟያ ዕቅድ ማሰባሰብ፣የተሰበሰበውን የማሟያ ዕቅድ መሠረት በማድረግ ክፍት መደቦችን በበጀት መደገፉን በማረጋገጥ በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የሰው ኃይል በደረጃ ዕድገት፣ በቅጥር፣ በዝውውር እና በምደባ ማሟላት፣ከተለያዩ መዋቅሮች የሚመጡ ቅጥር፣ ምደባ፣ ዝውውርና ደረጃ ዕድገት አግባብነቱን መርምሮ/አጣርቶ/ ለሚመለከተው ክፍል ማስተላለፍ፡፡
የሠራተኞችን ጥቅማ ጥቅም ማስከበር:- ደንብና መመሪያዎችን በጠበቀ መልኩ የሰራተኞችን ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞችን ማለትም የደረጃ ዕድገት የእርከን ጭማሪ የደንብ ልብስ እንዲሁም ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን ማስከበር፡በሥራ ፀባያቸው ምክንያት የደንብ ልብስ ለተፈቀደላቸው ሠራተኞች የደንብ ልብስ መሰጠቱን መከታተል፣
የዲሲኘሊን ጉዳዮችን በመመርመር ተፈጻሚ ማድረግ:- የዲሲኘሊን ጉዳዮች ሲቀርቡ ቀላልና ከባድ መሆኑን በመለየት በመመሪያው መሠረት ተፈጻሚ ማድረግ፣ የዲስፕሊን ኮሚቴዎችን በአዲስ መልክ እንዲቋቋሙ ማድረግ፡፡
የጋራ አገልግሎት ተግባራት በአግባቡ መፈፀማቸውን መከታተልና መደገፍ:-ለጋራ አገልግሎት ተግባራት የሚውሉ ቁሣቁስ እና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች እንዲሟላ ማድረግ፣በጋራ በመስራት ክፍተቶችን መሙላት፣የሥራ ድርሻን መከፋፈል፣የመ/ቤቱን ህንጻና ክፍሎች መብራት፣ ቧምቧና ሌሎችንም ወቅታዊ እድሣትና ጥገና መከታተል፣ የመ/ቤቱን ተሽከርካሪዎች በጥንቃቄ መያዛቸውንና አገልግሎት መስጠታቸውን መከታተላል ጉድለት ሲታይባቸው ለሚመለከተው ክፍል ማሳወቅ፡፡የመ/ቤቱን ግቢ እንዲሁም ክፍሎች በቂ ጥበቃና ቁጥጥር መደረጉን መከታተል፣ የመ/ቤቱንና የቤተ-መንግስት ግቢ ውበት የተጠበቀ እንዲሆን መከታተል፣ የመ/ቤቱን ግቢ፣ ክፍሎችና የመፀዳጃ ቤቶች በተገቢው ሁኔታ መፀዳታቸውን መቆጣጠር፣ ወደ መ/ቤቱ የሚመጡ ተገልጋዮቻችንን በአግባቡ በኢንፎርሜሽን ዴስክ ኦፊሰር መስተናገዳቸውን ክትትል ማድረግ፣
ሰራተኞችን በማትጋት ከፍተኛ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ማድረግ:- ሰራተኞችን ሊያተጉ የሚችሉ ስልቶችንና ስልጠናዎችን በማዘጋጀት ግንዛቤ እንዲያገኙ ማድረግ፤ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡትን ሠራተኞች በመለየት ማትጊያ እንዲሰጣቸው ለሚመለከተው ማቅረብ፣ አደረጃጀትን በአዲስ መልክ በማዋቀር የለውጥ ሠራዊት በዳይሬክቶሬቱ ማፍራት በቲሞች ውስጥ ሥራን በመገምገምና ክፍተትን በመለየት ያልበቁ ፈጻሚዎችን የማብቃት ሥራ መስራት፣ዕቅድን በአግባቡ ማቀድና ተግባራዊነቱን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣ ሣምንታዊ የክንውን ሪፖርትን ማዘጋጀት፣ በቲም የተደራጀውን የለውጥ ሰራዊት በማጠናከር ግንባር ቀደሞችን የመለየት ሥራ መስራት፣ በቲም ውስጥ በቡድን የመስራት ባህልን ማዳበር፣ የጡረታ መለያ ቁጥር የሌላቸውን በመለየት ቁጥርና ዐቅል ካርድ እንዲኖራቸው ማድረግ
ቁጥር የሌላቸውን የፅ/ቤቱ ሠራተኞችና ተሿሚዎች መለየትና ቁጥር እንዲኖራቸው አስፈላጊ የሆኑ የጡረታ ቅጽ በማስሞላት ከሚመለከተው ተቋም ጋር በመጻጻፍ ቁጥር እንዲያገኙ ማድረግ፣ የጡረታ መለያ ቁጥር ያላቸውን ሠራተኞች የዐቅል ካርድ ከኤጀንሲው እንዲያገኙ ማድረግ፣
የአገልግሎት ማቋረጥ ጥያቄን ተቀብሎ ማስተናገድ:- በተለያየ ምክንያት ማለትም በጡረታ፣ በሞት፣ በገዛ ፍቃድ፣ በዝውውር ሥራ በመልቀቅ እንዲሁም በህመም ምክንያት የአገልግሎት ማቋረጥ ጥያቄ ሲቀርብ ደንብና መመሪያው በሚፈቅደው መሰረት ተፈጻሚ ማድረግ፣
በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ጥራትና ቅልጥፍናን ማሳደግ:- የመረጃ አሰባሰብ አያያዝና አደረጃጀት ተግባራዊ ማድረግ፣ የፐርሶኔል መረጃን በተገቢው መልኩ ማደራጀት፣ ወደ መ/ቤቱ ተዛውረው የሚመጡ ተሿሚና የሰራተኞች ፋይል ካለበት ማስመጣትና በሚመለከተው የሥራ ሂደት እንዲደራጅ ማድረግ፣ መረጃዎችን ሙሉ በሙሉ ለአጠቃቀም በሚመች መንገድ ኮምፒውተራይዝ ማድረግ፣
የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት የአፈጻጸም ክህሎት ማሰደግ:- ለመ/ቤቱ ሠራተኞች፣ ለታችኛው መዋቅርና አስፈላጊ በሆኑ በአሰራር ማንዋሎች ላይ ግንዛቤ እንዲያገኙ ስልጠና መስጠት፣ መሠረት በዓመት ሁለት ጊዜ ቼክሊስት በማዘጋጀት መደገፍ፣ በተደረገው ድጋፍ መሠረት ፊትና ኋላ የወጡትን በመለየት ግብረ-መልስና እውቅና መስጠት፣
